በጅጅጋ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።

TIKVAHETHMAGAZINEneutral2026-07-23 11:22:58 UTC
AdYour ad here[email protected]

በጅጅጋ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ። በጅጅጋ ከተማ በካራማራ ክፍለ-ከተማ ልዩ ስሙ 10ኛ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ማምሻውን በተከተሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። አደጋውን ያደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ 3-85725 ET የሆነ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ሲሆን በአደጋው ህይወታቸው ካለፉ 7 ሰዎች መካከል 5 ወንዶች ሲሆኑ 2ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ተብሏል። አደጋው እንደደረሰ የአምቡላንስ ድንገተኛ አደጋ ደራሽ ሰራተኞች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የቪአይፒ ፀጥታ አካላት በፍጥነት በስፍራው በመገኘት ጉዳት የደረሰበትን ህጻን ወደ ህክምና ተቋም ያጓጓዙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል ብለዋል። ፖሊስ የአደጋውን ዝርዝር ምርመራ ውጤት በቀጣይ ለህዝብ ይፋ…

Read the full story at tikvahethmagazine ↗
AdYour ad here[email protected]