የጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ሥራ ሊያቆሙ መሆኑን አሣውቀዋል።
የጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ሥራ ሊያቆሙ መሆኑን አሣውቀዋል። የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር የታሪፍ ማሻሻያ ጥያቄን ምላሽ ባለማግኘቱ አባላቱ ከገበያ ሊወጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ማህበሩ ከትራንስፖርት፣ ንግድና ነዳጅ ቁጥጥር መስሪያ ቤቶች ጋር ጥናት አቅርቦ ምላሽ ማጣቱንም ገልጿል። አሁን ባለው የነዳጅ ፍላጎት መጨመር፣ የመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ መናር እና ድርብ ጫናዎች ምክንያት ሥራውን መቀጠል አስቸጋሪ ሆኗልም ተብሏል። በተጨማሪም ባለንብረቶች እውቅናቸው ውጪ በሹፌሮች በሚፈጸም የኮንትሮባንድ ወንጀል ምክንያት ተሽከርካሪና ነዳጅ እየተወረሰባቸው እንደሚገኝም ተናግረዋል። ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗