ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ከ215 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ።
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ከ215 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ። ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት ዓመቱ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰዋል። በተለይም የኔትወርክ ተደራሽነት እና ዘመናዊነትን ለማሻሻል በበጀት ዓመቱ 603 አዲስ የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎች ተገንብተው ወደ አገልግሎት ማስገባት ተችሏል። እንደሀገርም የሞባይል ጣቢያዎች ብዛት 10 ሺህ 613 ደርሷል ብለዋል። 195 የገጠር ሞባይል ጣቢያዎችን በመገንባት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የገጠር ማኅበረሰብን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ያሉት ሥራ አሥፈፃሚዋ በበጀት ዓመቱ ፈጣን የ5G አገልግሎትን 33 ከተሞች እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል። ኢትዮ ቴሌኮም እንደሀገር…
Read the full story at amharamassmedia ↗