ጀኔራሉ የት ገቡ?

WASULIFEneutral2026-07-23 15:33:24 UTC
AdYour ad here[email protected]

ጀኔራሉ የት ገቡ? የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በመቀሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሰወራቸው ተሰማ። ​እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ መኖሪያ ቤታቸውን በጥበቃ ተሽከርካሪዎች ከበበው የነበሩ ጥበቃዎችና ሰራተኞች ከምሽቱ ጀምሮ ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል ተብሏል። ጄነራሉ ከቀናት በፊት ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር እንዳይገናኙ በትግራይ ጸጥታ ቢሮ ተከልክለው እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ስለ ደህንነታቸው ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ይታወቃል። ​በፌደራል መንግሥት ከተሾሙ በኋላ በሕወሓት ከኃላፊነታቸው የተነሱት ጄነራሉ፤ ከድርጊቱ በፊት ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ለመገልበጥ የሚደረግ ሙከራ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት እንደሚያስገባ አስጠንቅቀው ነበር። ​በሕወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል የፖለቲካ ውጥረት በነገሰበት…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]