የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የአንድ በርሜል ዋጋ ዳግም ከ100 ዶላር በላይ ተሻገረ።
የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የአንድ በርሜል ዋጋ ዳግም ከ100 ዶላር በላይ ተሻገረ። በመካከለኛው ምሥራቅ ዳግም ባገረሸው ግጭት ሳቢያ የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በበርሜል በሐምሌ ወር ብቻ የ30 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ዳግም ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። ይህ ከፍተኛ ጭማሪ በተለይም የአሜሪካ ጦር ላለፉት 12 ቀናት በኢራን ግዛት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባዎችን ማካሄዱንና ኢራንም በአጸፋው በቀጠናው ሀገራት ላይ የምትሰነዝረው ጥቃት ተከትሎ የተስተዋለ ነው። በተመሳሳይ ከቀናት በፊት በየመን የሚንቀሳቀሱት እና በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕር በሚንቀሳቀሱ ሁለት የሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ሚሳኤልና ድሮን በመጠቀም ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጭማሪ ተስተውሏል። በተለይ የሁቲ አማጽያን በቀይ ባህር በሚገኘውና በቀን ከ7 ሚሊዮን በርሜል በላይ የነዳጅ ዝውውር…
Read the full story at tikvahethmagazine ↗