"የጋራ ተጠቃሚነታችን የሚረጋገጠው የሌሎችንም ሕመም መታመም ስንጀምር ነው"
"የጋራ ተጠቃሚነታችን የሚረጋገጠው የሌሎችንም ሕመም መታመም ስንጀምር ነው" በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ግለሰባዊ እና ማኅበረሰባዊ ግጭቶችን በመከላከል እና በማስወገድ ማኅበረሰባዊ ሰላም እና አንድነትን የሚጠብቁበት ጥበብ እየተካሄደ ለሚገኘው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ወሳኝ ልምድ የሚወሰድበት ነው። የሀገር ሽማግሌዎች የተጣሉ ወገኖችን ለማስታረቅ በመጀመሪያ ጠበኞችን ፊት ለፊት ከማገናኘታቸው በፊት ሁሉንም ለየብቻ በማነጋገር እና ሀሳባቸውን በማዳመጥ ስሜታቸውን ያረግባሉ። እውነተኛ ፍላጎታቸው ምን እንደኾነም በውል ይረዳሉ። ከዚያም ራሳቸውን ከስሜት እንዲያስወጡ፤ ሽማግሌ የሚላቸውን እንዲቀበሉ እና ልባቸውን ለዕርቅ እና ለይቅርታ ዝግጁ እንዲያደርጉም አደራ ይሰጧቸዋል። መቸም ሰው ከግጭት ይልቅ በሰላም መኖርን መሻቱ ተፈጥሯዊ ሥሪቱ ነውና…
Read the full story at amharamassmedia ↗