"የክረምት በጎ ፈቃድ እርስ በእርስ የምንተጋገዝበት እና በጎነትን የምናሳይበት ነው” ዶክተር መቅደስ ዳባ
"የክረምት በጎ ፈቃድ እርስ በእርስ የምንተጋገዝበት እና በጎነትን የምናሳይበት ነው” ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የክረምት በጎ ፈቃድ ነጻ የሕክምና እና የምክር አገልግሎት መርሐ ግብር አስጀምረዋል። በበጎ ፈቃድ ተግባሩ ከ 30 በላይ የሕክምና ተቋማት ተሳታፊ ይኾናሉ ተብሏል። የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ሥራ አሥኪያጅ ዶክተር አብረሃም እሸቴ ሆስፒታሉ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት የክረምት በጎ ፈቃድ ነጻ የሕክምና እና የምክር አገልግሎት ይሠጣል ብለዋል፡፡ በዚህ መርሐግብር ከ120 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታሰቡንም ገልጸዋል። ነጻ ሕክምናው ከፍተኛ የዲያግኖስቲክ አገልግሎት እና ቀዶ ሕክምናን የሚያካትት መኾኑንም ተናግረዋል። በመርሐ ግብሩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ እርስ በእርስ…
Read the full story at amharamassmedia ↗