ቀይ ባሕር
ቀይ ባሕር ኢራን በዚህ ወር የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አዛዦችን፣ ወታደራዊ አማካሪዎችን እና ከሚሳዔልና ድሮን ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶችን ወደ የመን መላኳን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደ ዘገባው፣ ይህ እርምጃ በቀይ ባሕር የመርከብ ጉዞዎችን ለማስተጓጎል የሁቲዎችን አቅም ለማጠናከር የታሰበ ነው። ሮይተርስ እንደገለጸው፣ ከ10 እስከ 21 የሚደርሱ የአብዮታዊ ዘብ አዛዦች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ወደ የመን ተጓጉዘዋል፣ ለሁቲዎችም በአዲስ የሚሳዔል ሥርዓት ላይ ስልጠና እንዲሰጡ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል። በሌላ በኩል ኢራን እና ሁቲዎች እነዚህን ክሶች በማስተባበል፣ ወደ የመን የተላኩ ሰዎች ሲቪል ተሳፋሪዎች እንጂ ወታደራዊ ባለሙያዎች አይደሉም ብለዋል። ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗