የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በየዓመቱ ሐምሌ 19 በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በየዓመቱ ሐምሌ 19 በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል። የከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር መሳፍንት ሙሉጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የሚያስፈልጉ የጸጥታና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀዋል። በዓሉ በሳምንቱ መጨረሻ እንዲሁም በክረምት ወቅት መከበሩን ተከትሎ ከመላ ኢትዮጵያ እና ከውጭ አገራት በርካታ ምዕመናን ወደ ሀዋሳ እንደሚመጡ ጠቅሰው፣ እንግዶች በከተማው ሰላማዊና ምቹ ቆይታ እንዲያደርጉ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗