" በአካባቢው ዳገታማና ጠመዝማዛ መንገዶች ስለሚበዙ ጥንቃቄ አድርጉ " - ፖሊስ

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-24 15:16:51 UTC
AdYour ad here[email protected]

" በአካባቢው ዳገታማና ጠመዝማዛ መንገዶች ስለሚበዙ ጥንቃቄ አድርጉ " - ፖሊስ የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ዝግጅት ተጠናቋል። የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰላምና በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊውን የጸጥታ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። የበዓሉ ታዳሚዎች ጉዞ ሲያደርጉ ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል። በአካባቢው ዳገታማና ጠመዝማዛ መንገዶች በመብዛታቸው እና ወቅቱ ክረምት በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ሕግና ደንብን በመከተል በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል። #ኢዜአ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]