ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምናልባት ከአንድ ጨዋታ በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል እንደሚችል ተዘግቧል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምናልባት ከአንድ ጨዋታ በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል እንደሚችል ተዘግቧል። የ 5 ጊዜ ባሎንዶር አሸናፊዉ ፖርቱጋላዊው ጥበበኛ በወርሃ መስከረም ሀገሩ ዌልስን በስፖርቲንግ ሊዝበን ሜዳ የምታስተናግድ ሲሆን ይህም ምናልባት የሮናልዶ የመጨረሻው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተገምቷል። በስፖርቲንግ ሊዝበን የእግርኳስ ህይወቱን ለጀመረዉ ሮናናልዶ በዛዉ ስታዲየም ላይ የብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ጨዋታው ሊሆን ይችላል ተብሏል። ሮናልዶ እስካሁን በ 233 ጨዋታዎች 146 ግቦችን አስቆጥሮ የዩሮ ዋንጫንም ለሀገሩ አምጥቷል። #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗