የ2019 በጀት ዓመት የጡረታ መታወቂያ ዕድሳት ተጀምሯል።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-24 15:44:37 UTC
AdYour ad here[email protected]

የ2019 በጀት ዓመት የጡረታ መታወቂያ ዕድሳት ተጀምሯል። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር፣ የ2019 በጀት ዓመት የጡረታ መታወቂያ ዕድሳት ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ መጀመሩን ገልጿል። የመታወቂያ ዕድሳት አገልግሎቱ፣ እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ በመሆኑ የጡረታ ባለመብቶች በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ጽ/ ቤቶች ወይም በዕድሳት ማዕከላት በመቅረብ መታወቂያቸውን እንዲያድሱ ጥሪ ቀርቧል። ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በነፃ ስልክ መስመር 8926 መደወል እንደሚቻል ተገልጿል። Via @TikvahethMagazine

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]