በኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ75 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ75 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ከ72 ነጥብ 65 በመቶ ወደ 75 ነጥብ 59 በመቶ ማሳደግ መቻሉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ84 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ መድረሱን ነው የገለጹት፡፡ በበጀት ዓመቱ ብቻ ከ4 ነጥብ 85 ሚሊየን በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ የትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከነበረበት 43 በመቶ ወደ 45 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ የውሃ ተቋማት የብልሽት ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 12 በመቶ የቀነሰ ሲሆን÷ የውሃ ብክነት መጠንን ደግሞ ከ29 በመቶ ወደ 27…
Read the full story at tikvahethmagazine ↗