በፈረንሳይ እና ስፔን የተቀሰቀሰዉ ከባድ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን ቀጥሏል
በፈረንሳይ እና ስፔን የተቀሰቀሰዉ ከባድ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን ቀጥሏል የፈረንሳይ ባለስልጣናት በደቡብ ምዕራብ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኘውን የካፕ ፌሬት ባሕረ ገብ መሬት በሙሉ ነዋሪዎች ለቀዉ እንዲወጡ አዘዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በጀልባ ከአካባቢው ወጥተዋል። የእሳት አደጋ ተከላካዮች በጊሮንዴ ክልል ለቀናት የቆየውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት እየተጉ ቢሆንም የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዉ ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ በሳውሞስ የተከሰተው እሳት 8 ሺህ 700 ሄክታር መሬት በእሳት ቃጠሎው አውድሟል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ አቅራቢያ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ሰደድ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ የስፔን መንግስት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አውጇል። በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ማክሰኞ ዕለት በቦርዶ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በተነሳ…
Read the full story at addis_news ↗