የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ ድጋፎቼን ለመቀጠል 182 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ ድጋፎቼን ለመቀጠል 182 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ። ድርጅቱ፣ በተያዘው አውሮፓዊያን ዓመት ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታዎቹ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ላይ ገልጧል። እስከ ቀጣዩ ነሃሴ ወር በአገሪቱ ውስጥ የስብዓዊ እርዳታውን ለማስቀጠል ለእያንዳንዱ የምግብ እህል ተረጂ ከመደበው መደበኛ ራሽን ላይ 60 በመቶውን ለመቀነስ እንደተገደደም ድርጅቱ ጠቅሷል። የአገሪቱ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ከፍተኛ የኾነው፣ ግጭት፣ መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ እና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ጫናዎች በተጋላጭ ማኅበረሰቦች ላይ በሚያሳድሩት ጉዳት ሳቢያ ነው ብሏል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗