መረጃ‼️
መረጃ‼️ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የአበባ፣ የፍራፍሬ እና የአትክልት ምርት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አገኘች። አገሪቱ በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ ካገኘችው 490 ሚሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገቢ ውስጥ፣ የአበባ ምርት 412 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ከፍተኛውን ድርሻ መያዙን ግብርና ሚንስቴር አስታውቋል። ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የአትክልት ምርቶች 57 ሚሊዮን ዶላር ሲገኝ፣ ከፍራፍሬ ምርቶች ደሞ 21 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል፡፡ ኾኖም አገሪቱ ይህን ገቢ ያገኘችው ምን ያህል ቶን ምርቶች ለውጭ ገበያ አቅርባ እንደሆነ ሚንስቴሩ አልጠቀሠም። ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት 357 ሺሕ 457 ቶን አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ለውጭ ገበያ በማቅረብ፣ 575 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳለች ተብሏል፡፡ @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗