ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፣ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን!!!

ADDIS_NEWSneutral2026-07-25 16:47:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፣ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን!!! ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ”…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]