“ ተፈናቃዮችን መመለስ ሽፋን ነው፤ ዋና ዓላማው ሥልጣን መያዝ ነው ” - አቶ ጌታቸው ረዳ

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-25 20:00:26 UTC
AdYour ad here[email protected]

“ ተፈናቃዮችን መመለስ ሽፋን ነው፤ ዋና ዓላማው ሥልጣን መያዝ ነው ” - አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፥ በህወሓት አመራሮች እና በተለይም በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ላይ በርካታ ከባድ ውንጀላዎችን በማቅረብ፣ ቡድኑ ትግራይን ወደ አዲስ ጦርነት ለመመለስ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው እንደገለጹት፤ የህወሓት አመራር ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ወታደራዊ ትብብር ለመፍጠር እየሠራ ሲሆን፣ በተለይም ዶ/ር ደብረጽዮን ወደ ኤርትራ በማቅናት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ለጦርነት ድጋፍ፣ የጦር ቁሳቁስና ጥይት መጠየቃቸውን በመግለጽ ወንጅለዋል። በተጨማሪም የህወሓት አመራር የትግራይ ወጣቶችን ለአዲስ ጦርነት በማሰባሰብና በመመልመል ወደ ግንባር ለመላክ እየተዘጋጀ መሆኑን ከሌሎች ታጣቂ ቡድኖች…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]