የሚሲ አባት ህክምና የሚከታተሉበት ተቋም መዘረፉ ተነገረ !
የሚሲ አባት ህክምና የሚከታተሉበት ተቋም መዘረፉ ተነገረ ! የሊዮኔል ሜሲ ወላጅ አባት ጆርጅ ሜሲ የጤና እክል እንዳጋጠማቸው ከዚህ በፊት መነገሩ አይዘነጋም። አሁን ላይ ጆርጅ ሜሲ ህክምናቸውን የሚከታተሉበት ተቋም በዘራፊዎች መዘረፉ ተነግሯል። ዘራፊዎቹ ከህክምና ተቋሙ ኮሚፒዩተሮችን ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መዝረፋቸው ተዘግቧል። የአካባቢው ባለስልጣናት ከፍተኛ ክትትል ቢያደርጉም የተወሰዱትን እቃዎች ማስመለስ አልቻሉም ተብሏል። ዘራፊዎቹ ያንን ያደረጉት እቃውን ለመውሰድ ነው ወይስ የሊዮኔል ሜሲን አባት ህክምና መረጃ ለማግኘት የሚለው እየተጣራ ይገኛል ተብሏል። የሊዮኔል ሜሲ አባት የህክምና ታሪክ በኮሚፒዩተሮች ውስጥ ስለመኖሩ ከተቋሙ አልተረጋገጠም። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗