#ቅዱስገብርኤል
#ቅዱስገብርኤል #ሐምሌ19 በሀዋሳ ከተማ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ንግሥ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል። ፖሊስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ቅንጅታዊ ሥራ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ መደረጉን ገልጾ፣ በበዓሉ ወቅት በስርቆት የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች ከ2 ዓመት ቀላል እስራት እስከ 3 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን ገልጿል። መምሪያው ለበዓሉ ሰላማዊ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፀጥታ ኃይሎች፣ የከተማው ነዋሪዎች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ምስጋና አቅርቧል። ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗