የአሸናፊዎች አሸናፊ ውጊያ ይደረጋል‼️
የአሸናፊዎች አሸናፊ ውጊያ ይደረጋል‼️ ህወሃት የ 1983 ታሪክን እንደግማሁ እያለ ነው። የሕወሓት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ) ከሰሞኑ በአንድ መድረክ ላይ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሁን ከተጣመርናቸው ኃይሎች ጋር መዋጋታችን አይቀርም ብለዋል፡፡ የሀላፊዋ ንግግር የጽምዶ ኃይሎችን የትብብር መሰረት የሚያናጋ ነው ተብሏል፡፡ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ቃል በቃል የተናገሩ፡- ‹‹ዋናው ነገር ብልፅግናን ለመጣል ፍላጎት ያሳይ እንጂ የትኛውም ስብስብ እርስ በራሱ እሳትና ጭድ ቢሆንም እንኳን አብረን እንሰራለን። ብልፅግናን ከጣልን በኃላ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመለየት ሌላ ዙር ፍልሚያ ይኖረናል። ለዚህም እየተዘጋጀን ነው፤ ይህ በተለያየ መልክ የተጀመረውን ትብብራችንን ስናየው የተለያየ ፍላጎት ያለን ሃይሎች ሆነን ነው ትብብር እየፈጠርን ያለነው።…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗