ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር በዋሺንግተን ለመምከር አቀኑ‼️
ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር በዋሺንግተን ለመምከር አቀኑ‼️ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በከፍተኛ ደረጃ ውይይት ለማድረግ ወደ ዋሺንግተን በማመራት ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። በሁለቱ መሪዎች ምክክር ወቅት የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናዊ ደህንነት እና ከኢራን ጋር የተያያዘው ውጥረት በዋና አጀንዳነት እንደሚዳሰሱ ይጠበቃል። የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ኔታንያሁ ዋሺንግተን በሚቆዩበት ወቅት አሜሪካ በቴህራን ላይ የምታደርገውን ጠንካራ ወታደራዊ ጫና አጠናክራ እንድትቀጥል እንደሚጠይቁ ተመልክቷል። በተጨማሪም ሂዝቦላህን ጨምሮ በኢራን የሚረዱ የታጠቁ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገው ጥረት እንዲፋጠን ጥሪ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ጉብኝት እየተካሄደ ያለው በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ወታደራዊና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በከፍተኛ…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗