መድኃኒቱን የተላመደ የድብርት በሽታን ማከም የሚያስችል ማሽን ስራ ላይ ማዋሉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ

ZENA24NOWneutral2026-07-27 16:08:25 UTC
AdYour ad here[email protected]

መድኃኒቱን የተላመደ የድብርት በሽታን ማከም የሚያስችል ማሽን ስራ ላይ ማዋሉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ የኮሌጁ የአእምሮ ሕክምና እና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር መስከረም አበበ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ኮሌጁ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ማሽን አስተዋውቋል ።ኮሌጁ ቲኤምኤስ የተሰኘውንና ድብርትን የሚያክም አዲስ ማሽን ማስተዋወቁን ገልፀዋል። በመድኃኒት ሕክምና መልስ አልሰጥም ላለ የድብርት ወይም የድባቴ ሕመም ማሽኑ ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉን የገለፁት ዶክተር መስከረም ለሌሎች የአእምሮ ሕመም ዓይነቶች ጭምር አገልግሎት መስጠት እንደሚችል አብራርተዋል።አእምሮን ለማነቃቃትና ድብርትን ለማከም የሚረዳው አዲሱ ማሽን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥም የመጀመሪያው ነው። እስካሁን ባለው ሂደት ከ10 በላይ ታካሚዎች ህክምና…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]