የጦርነትና የግጭት ሁኔታዎች ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ትልቅ ፈተና መሆናቸው ተጠቆመ
የጦርነትና የግጭት ሁኔታዎች ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ትልቅ ፈተና መሆናቸው ተጠቆመ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች እና ጦርነቶች ለጤና አገልግሎቱ ችግር መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር ነው ያስታወቀው። በተለይም የእናቶች እና ህፃናት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት መፍጠራቸውን በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና ቤተሰብ ዕቅድና የአፍላ ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ገልፀዋል። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረው ጦርነትና አሁን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች የጤና ባለሙያዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ ከማድረጋቸውም በላይ የግብዓትና የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል። ዶክተር አለማየሁ እንዳሉት፥ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች እናቶች ለሞትና ለከፍተኛ ስቃይ የሚዳረጉበት ዕድል ሰፊ…
Read the full story at addis_news ↗