በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ አቅራቢያ በሚገኘው ዱአዞን በተካሄደ ዘመቻ ወደ 4 ቶን የሚጠጋ ኮኬይን በቁጥጥር ስር ውሏል
በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ አቅራቢያ በሚገኘው ዱአዞን በተካሄደ ዘመቻ ወደ 4 ቶን የሚጠጋ ኮኬይን በቁጥጥር ስር ውሏል እንደ ሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ የዕፆቹ ዋጋ እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ተገምቷል። በዚህ በሀገሪቱ ታሪክ ትልቁ በተባለው የዕፅ ዝውውር ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ታዋቂው የሰርቢያ ኪክቦክስ ተወዳዳሪ ስርጃን ሴሌሽ እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሴሌሽ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዳለውና ከሰርቢያ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚሰራጩ ወሬዎችን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ ተጠርጣሪው ምንም ዓይነት የዲፕሎማትነት ማዕረግ ወይም ፓስፖርት የሌለው መሆኑን ገልፇል። በፖሊስ ጥናት መሠረት ለዓመታት ሲሰራበት የነበረው ይህ የኮኬይን ዝውውር ወደ አውሮፓ ገበያ ለማስገባት የተዘጋጀ እንደነበር ተገልጿል።…
Read the full story at addis_news ↗