‎ከጣውላ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሠራው ወጣት።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-07-28 10:00:13 UTC
AdYour ad here[email protected]

‎ከጣውላ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሠራው ወጣት። ‎ ‎በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የተወለደው ወጣት አብነህ አቻምየለህ የፈጠራ ክህሎቱን የጀመረው ገና በልጅነቱ ነበር። በተለይም ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲያልፍ የወደቁ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በመጠገን የጀመረው ጉዞ በኋላ ላይ የፈጠራ ሥራውን እንዲያሰፋ ትልቅ መንገድ ከፍቶለታል። ‎ ‎ሥራ አጥነትን በፈጠራ እና በትግል ማለፍ እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጠው ወጣቱ ከጣውላ የሠራቸውን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያዎች (ዲቫይደሮች) ወደ ገበያ ማስገባት ችሏል። ‎ ‎ወጣቱ መጀመሪያ ላይ ያገለገሉ የፕላስቲክ «ኪቶ ጫማ» ሶሎችን በመሠብሠብ ለኮምፒውተር እና ለተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማከፋፈያ የሚኾኑ ዲቫይደሮችን ይሠራ እንደነበር ተናግሯል፡፡ በሂደትም ወደ ሀገር በቀሉ ጣውላ በመቀየር ጥራታቸው የተረጋገጡ ምርቶችን ማምረት ጀምሯል። ‎…

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]