በትግራይ ክልል ለተወሰነ ጊዜ የታየው የክረምት ዝናብ እጥረት መሻሻሉን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ለተወሰነ ጊዜ የታየው የክረምት ዝናብ እጥረት መሻሻሉን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ከሐምሌ 18/2018 ዓ.ም. ጀምሮ ቀደም ሲል ዝናብ ያላገኙ 176 የገጠር ቀበሌዎችን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎች ዝናብ መጣሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ በማዕከላዊ ዞን ወረዳ ቀይሕ ተኽሊና በአካባቢው በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች የጣለው በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ 12 ቤቶችን በማፍረስ 2,134 አባወራዎችን አፈናቅሏል። በተጨማሪም 1,059 ሄክታር የእርሻ ሰብልና 115 ሄክታር የመስኖ አትክልት ማሳ ወድሟል፤ የ12 ዓመት ሕፃን ሕይወት ሲያልፍ 387 የቤት እንስሳትም መሞታቸው ተመዝግቧል። መረጃው ከአካባቢው ምንጮች የተገኘ ሲሆን፣ የዝናቡ መሻሻል ለእርሻ ተስፋ ቢፈጥርም በአንዳንድ ስፍራዎች ከባድ ጉዳት ማስከተሉ ተገልጿል። ሃምሌ 21 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
Read the full story at tikvahethiopia ↗