አባት ኾይ የሀገር ፍቅር እንደምን ያለች ናት?
አባት ኾይ የሀገር ፍቅር እንደምን ያለች ናት? ሞትን የናቁላት፤ በጠላቶችዎ ፊት ስለ ፍቅሯ የመሰከሩላት፤ በሞት አፋፍ ላይ ኾነው በጽናት የቆሙላት፤ በጥይት አረር የተጠበሱላት፤ እስከ ሞት ድረስ የወደዷት፤ ቃል ኪዳንም ያስቀመጡላት፤ ትውልድ ሁሉ በጠላት እንዳይገዛ አደራ ያሉባት አባት ኾይ የሀገር ፍቅር እንደምን ያለች ናት ? መከራን የታገሱላት፣ በሀሰተኞች ፊት ቆመው መራራዋን ፍርድ የተቀበሉላት፤ አስከፊዋን ጽዋ የተጎነጩላት፣ ሀገሬን አትንኩ እያሉ ሊገድሉዎት ከቆሙ ጠላቶቿ ፊት በድፍረት የቆሙላት ሀገርዎትን እንዴት አድርገው ቢወድዷት ነው ? ሞትን ሲያዩት፤ የገዳዮችን መሻኮል ሲመለከቱት፤ የጠላቶችዎን ጭካኔ እና በሀገሬው ሰው የሚደርሰውን በደልና ግፍ ሲታዘቡት ምን ተሰምቶዎት ይኾን ? በጠላቶችዎ ጭካኔ እስኪሞቱ ድረስ ስንት ማዕልትን እና ስንት ሌሊቶችን ለሀገርዎ እና ለሃይማኖትዎ…
Read the full story at amharamassmedia ↗