የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በነጻ ህክምና የ431 ታካሚዎችን የዓይን ብርሃን መመለሱን አስታወቀ
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በነጻ ህክምና የ431 ታካሚዎችን የዓይን ብርሃን መመለሱን አስታወቀ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተደረገ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ነጻ የአይን ህክምና የ4 መቶ 31 ታካሚዎችን የዓይን ብርሃን መመለስ መቻሉን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልጀባር አብደላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በተጠናቀቀው የ2018 በጀት አመት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ሰው ተኮር ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል።ይህ የነፃ ህክምናና ምርመራ አገልግሎት ከሀበሺስታን ዴቬሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን ጋር በመተባበር ተከናውኗል። በተደረገው ነጻ የአይን ምርመራና ህክምና ለ7 ሺህ 4 መቶ 78 ታካሚዎች ምርመራ በማድረግ የአይን ሞራ ግርዶሽ ለተገኘባቸው 4 መቶ 31 ታካሚዎች የአይን ሞራ…
Read the full story at zena24now ↗