ተጨዋቾቹ ጠፉ‼
ተጨዋቾቹ ጠፉ‼ ወደ ስዊድን ሀገር ለእግር ኳስ ጨዋታ ሄደው 20 ኢትዮጵያውያን ከነ ቡድን መሪያቸው በዚያው መጥፋታቸው ተሰማ። በስዊድን በተካሄደው የጎቲያ ካፕ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ከተሳተፉ ከ20 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች እና የቡድን መሪዎች በዚያው መጥፋታቸውን የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል። ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 17 የሚሆኑት እነዚህ ታዳጊዎች በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ያረፉበት ትምህርት ቤት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለቀው መሄዳቸው ተውቋል። የስዊድን ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ግለሰቦቹ ወደ ኢትዮጵያ አለመመለሳቸውን እና መጥፋታቸው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እንጂ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ምልክት እንደሌለው ገልጿል። እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በስዊድን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስለ ጉዳዩ የሰጡት አስተያየት የለም። #WasuMohammed video…
Read the full story at wasulife ↗