በርካታ ወጣቶችን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውርና ግፍ ሲፈጽም የነበረው አደገኛ ወንጀለኛ አድነው ባሻው በቁጥጥር ሥር ዋለ!

ADDIS_NEWSneutral2026-07-30 09:30:21 UTC
AdYour ad here[email protected]

በርካታ ወጣቶችን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውርና ግፍ ሲፈጽም የነበረው አደገኛ ወንጀለኛ አድነው ባሻው በቁጥጥር ሥር ዋለ! የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር ባደረገው የተቀናጀ ክትትል፣ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ላይ ከባድ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የቆየውን አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ ሀገር በቁጥጥር ሥር በማዋል ለሕግ ተጠያቂ እንዲሆን ወደ ሀገር ውስጥ አምጥቶታል። እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ፣ ተጠርጣሪው ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች ወጣቶችን «ሕይወታችሁን ታሻሽላላችሁ» በሚል አጉል ተስፋ በማታለል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር ቆይቷል። ተጠርጣሪው ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺሕ እስከ 800 ሺሕ ብር የሚጠይቅ ሲሆን፤ ቅድመ ክፍያ 100 ሺሕ ብር…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]