ግብር ሊከፍሉ ነው‼️

ADDIS_REPORTERneutral2026-07-30 09:59:31 UTC
AdYour ad here[email protected]

ግብር ሊከፍሉ ነው‼️ በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነዉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዋስሁን በላይ ይህ ግብር በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ተሽከርካሪዎቹ በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ ስለሚንቀሳቀሱ በየዓመቱ የሚከፈል ይሆናል ብለዋል። ይህም ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ወይም ቦሎ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ እንደገለፁት ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ፣ አዳዲሶች ደግሞ ዝቅተኛ እንዲከፍሉ ሊደረግ ይችላል ተብሏል። ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]