በሀላባ ዞን የዉሃ አቅርቦት አናሳ መሆን ለዓይን ጤና ችግር ምክንያት ሆኗል ተባለ

ZENA24NOWneutral2026-07-30 16:35:42 UTC
AdYour ad here[email protected]

በሀላባ ዞን የዉሃ አቅርቦት አናሳ መሆን ለዓይን ጤና ችግር ምክንያት ሆኗል ተባለ በዞኑ የዓይን ህመም ለበርካታ ጊዜያት የቆየና ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ችግር መሆኑ ተገልጿል ። ችግሩን ለመቅረፍ የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።የሆስፒታሉ ምክትል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መለሰ ሙዳ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት በዞኑ የተስተዋለው የዉሃ አቅርቦት እጥረት ለዓይን ህመም ችግር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ነዉ። ይህንንም ችግር ለመፍታት ካለፉት ዓመታት በተሻለ መልኩ በገጠራማ አከባቢዎች የዉሃ አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራት በሚመለከታቸው አካላት እና በአጋር ድርጅቶች ትብብር እየተከናወነ ይገኛል።በቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል መደበኛ የዓይን ህክምና እየተሰጠ…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]