"ከአቅማችን በላይ የሆነ ግብር ተጥሎብናል፤ መስራት እንዳንችል እያደረገን ነው" ሲሉ የቁርጥ ግብር ከፋዮች ከፍተኛ ቅሬታ አቀረቡ።
"ከአቅማችን በላይ የሆነ ግብር ተጥሎብናል፤ መስራት እንዳንችል እያደረገን ነው" ሲሉ የቁርጥ ግብር ከፋዮች ከፍተኛ ቅሬታ አቀረቡ። በርካታ በክልል እና በከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የቁርጥ ግብር ከፋዮች ለ2018 ዓ.ም. የተተመነባቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ነጋዴዎቹ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ግብሩ በግዴለሽነት፣ በዘፈቀደ እና እጅግ መጨመሩን ገልጸዋል። አንዳንዶቹ የሚከፍሉት ግብር ከ25,000 ብር ወደ 180,000 ብር፣ እንዲሁም ከ10,000 ብር ወደ 50,000 ብር ማደጉን ጠቅሰዋል። ግብሩን በፍጥነት ካልከፈሉ የንግድ ቦታቸው እንደሚታሸግ እንደተነገራቸው እና አቤቱታ ለማቅረብ የሚሰማቸው ማጣታቸውንም ገልጸዋል። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የግብር ግምገማው በተጨባጭ የንግድ አቅም ላይ ተመስርቶ እንዲከናውን እና የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።…
Read the full story at wasulife ↗