#ETA
#ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ በተደረገው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ አርብ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት የውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ባለሥልጣኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ ባለሥልጣኑ በመመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ በተደረገው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡና ባለድርሻ አካላት እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም አስተያየታቸውን በኦንላይን እንዲሰጡ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗