የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ADDIS_NEWSneutral2026-07-31 08:59:48 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚዲያ ተቋማት ሕግና የሙያ ሥነ ምግባርን አክብረው መስራታቸውን እየተከታተለ ድጋፍና እርምት በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚሁ መሠረት፦ • አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና • አርትስ ቴሌቪዥን የተሰጣቸውን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ፣ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሬድዮ እና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር በተስተዋሉ ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ጥሰቶች ላይ ውይይቶች ያደረገ ቢሆንም ጉልህ ለውጥ ሳይታይ በመቅረቱ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያስታውቃል፡፡ ስለሆነም ጣቢያዎቹ በቀጣይ ሥራቸውን…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]