የአርሰናል ባለሀብቶች በቪኒሽየስ ዝውውር ጉዳይ በድንገት እጃቸውን አስገቡ።
የአርሰናል ባለሀብቶች በቪኒሽየስ ዝውውር ጉዳይ በድንገት እጃቸውን አስገቡ። ሪያል ማድሪድ የብራዚላዊውን ኮከብ ውል ለማራዘም ቢጥርም በደሞዝ ጉዳይ እስካሁን ድረስ አልተስማሙም። ቪኒሽየስ ውሉን የማያድስ ከኾነ ከአንድ ዓመት በኋላ ማድሪድ ድምቡሎ ሳያገኝ ተጫዋቹን ያጣዋል። ይህንን ክፍተት ተጠቅመው አርሰናሎች ተጫዋቹን ወደ ለንደን ለማስኮብለል እየሠሩ ነው። ያሆ ስፖርት እንደዘገበው የአርሰናል ባለቤቶች የክሮንኬ ቤተሰቦች ከቪኒሽየስ ወኪል"ሮክ ኔሽንስ" ጋር ተወያይተዋል። ባለሀብቶቹ ክለቡን በሱ ዙሪያ ለመገንባት ስለያዙት ኘሮጀክት እና በሳምንት እስከ 400ሺህ ፖውንድ ደሞዝ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ለወኪሉ አብራርተዋል። ያም ኾኖ የቪኒሽየስ ጁኒየር ተቀዳሚ ምርጫው የማድሪዱ ክለብ መኾኑን ዘገባው አመላክቷል። #አሚኮ #ስፖርት #ባሕር_ዳር #ሐምሌ_24_2018_ዓ_ም በንዋይ ሙሉጌታ…
Read the full story at amharamassmedia ↗