የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ከጎንደር ሁመራ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር ነው።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-07-31 12:20:40 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ከጎንደር ሁመራ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ወደ ሁመራ የበረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ለአሚኮ በላከው መግለጫ ጠቁሟል። የበረራ አገልግሎቱ ዘወትር ቅዳሜ ከጎንደር ወደ ሁመራ የሚደረግ ሲኾን ዘወትር ሰኞ ደግሞ ከሁመራ ወደ ጎንደር አገልግሎት ይሰጣል። አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎችን በማስፋት ሕዝብን ለማገልገል እንደሚሠራ የገለጸ ሲኾን ከጎንደር ሁመራ የተጀመረው አገልግሎትም ማኅበራዊ ግንኙነትን ከፍ የሚያደርግ ነው። #አሚኮ #ethiopianairlines #Ethiopia የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]