" ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶ የአለልኝ ገዳዮች ነፃ ከተባሉበት ወደ ማረሚያ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተላልፏል" - የአለልኝ አዘነ ቤተሰቦችና ወዳጆች

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-31 17:31:09 UTC
AdYour ad here[email protected]

" ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶ የአለልኝ ገዳዮች ነፃ ከተባሉበት ወደ ማረሚያ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተላልፏል" - የአለልኝ አዘነ ቤተሰቦችና ወዳጆች በቀድሞው የባህር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ የተጠረጠሩት የአለልኝ ሚስት አዴይ ጌታቸው እና የእህቷ ባል ሉንጎ ሉቃስ ጥፋተኛ ተብለው በሐምሌ 2017 ዓ.ም የ16 እና 15 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው ነበር። በኋላ ይግባኝ በመጠየቃቸው ባሳለፍነው ግንቦት ወር በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ይህን ውሳኔ ተከትሎ ቤተሰቡ የተሰማውን ከፍተኛ ቅሬታ መዘገባችን ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአለልኝ አዘነ ቤተሰቦች እና ጓደኞቹ ባገኘው መረጃ፣ ውሳኔውን ተከትሎ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቆ ተቀባይነት ማግኘቱን እና ትናንት ሐምሌ 23/2028 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ወላይታ ሶዶ ምድብ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]