መረጃ‼️
መረጃ‼️ በሳዑዲ ዓረቢያ አስተባባሪነት፣ 14 አገራት በቀይ ባሕር፣ ባብኤል መንደብና የኤደን ባሕረ ሠላጤ የንግድና የኢነርጂ አቅርቦት መስመር ደኅንነትን የሚያስጠበቅ ጥምር የመከላከያ ኃይል አቋቋሙ። ጥምረቱ፣ አባል አገራት መረጃ እንዲለዋወጡ፣ የዘመቻ እቅድ እንዲያወጡና የጋራ የባሕር ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው። ከአፍሪካ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ግብጽ እና ናይጀሪያ የጥምረቱ መስራቾች ኾነዋል። ከሌሎች መስራቾች መካከል ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና ፓኪስታን ይገኙበታል። ፍላጎቱ ያላቸው አገራት ጥምረቱን በማንኛውም ጊዜ መቀላቀል ይችላሉ ተብሏል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ እና ኢምሬቶች በጥምረቱ መስራችነት ካልተካተቱ የቀጠናው አገራት መካከል ናቸው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗