የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምቹ ሁኔታዎች ባሏቸው የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች ከዚህ ዓመት ጀምሮ የማታ በረራዎች እንደሚጀመር ገልጿል። 

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-01 17:24:59 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምቹ ሁኔታዎች ባሏቸው የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች ከዚህ ዓመት ጀምሮ የማታ በረራዎች እንደሚጀመር ገልጿል። " በሀገር ውስጥ የሥራ ሰዓት በአግባቡ ለመጠቀምና የመንገደኞችን ፍላጎት ለማርካት የማታ በረራዎችን ለማስፋፋት ታቅዷል " ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። " ኤርፖርቶች ማታ ለመስራት በምሽት መብረር የሚፈልግ መንገደኛ መኖር አለበት ፣ በአንድ ወቅት ባህር ዳር፣ ጎንደር እና መቐለ ጀምረን ነበር ነገር ግን እዛ ባለ የጸጥታ ሁኔታ የምሽት በረራውን ለጊዜው አቁመነዋል እንጂ መቀጠላችን አይቀርም " ነው ያሉት። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የክልል ኤርፖርቶች ላይ የመብራት ተከላ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ምቹ ሁኔታዎች ባሏቸው ኤርፖርቶች ከዚህ ዓመት ጀምሮ የማታ በረራዎች እንደሚጀመር አቶ መስፍን ጣሰው አሳውቀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]