#Update
#Update በቀድሞ የህወሓት አመራሮች የተመሰረተው ስምረት ፓርቲ፣ የትግራይ ሕዝብ የማይፈልገውና የማይመኘው አዲስ ወታደራዊ ግጭት ዛሬ ሌሊት መቀስቀሱን አሳውቋል። " ግጭቱን ማንና መቼ እንደጀመረው ለማወቅ አስቀድሞ ተዘጋጅቶ የወጣውን የኋላቀሩ ቡድን (ህወሓት) መግለጫ ከመስማት ይልቅ፣ ገለልተኛ አካላት የሚያደርጉትን የሳተላይት ክትትልና የክትትሉን ውጤት መጠበቅ ተገቢ ነው " ሲል ገልጿል። ፓርቲው፣ " አሁን የተከፈተው ጦርነት በውጭ ኃይሎች ፍላጎትና እቅድ የሚመራና የሚደገፍ ነው " ብሏል። " ሆኖም የጦርነቱ እቅድ በራሳቸው የጦርነት ነጋዴዎች አማካኝነት አስቀድሞ ምስጢሩ ታውቆ ያደረ በመሆኑ እንቅስቃሴው ገና ሳይስፋፋ የሚከሽፍ ነው " ሲል ጠቅሷል። አክሎም፣ " የዚህ አላስፈላጊ ግጭት ዋና ሰለባና የመከራው ተቀባይ እየሆነ ያለው የትግራይ ወጣት መሆኑ አሳዛኝ ያደርገዋል " ብሏል።…
Read the full story at tikvahethiopia ↗