የዝናብ እጥረት
የዝናብ እጥረት በትግራይ ክልል በማዕከላዊና ምስራቃዊ ዞኖች የሚገኙት የአበርገለ እና የኢሮብ ወረዳዎች እስካሁን የክረምት ዝናብ ባለማግኘታቸው፣ በ21 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት የሚኖሩ ነዋሪዎችና እንስሳት ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል። በአበርገለ ወረዳ የሚገኙ 13 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት እስካሁን የክረምት ዝናብ ያላገኙ ሲሆን፣ በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ 8 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ደግሞ የክረምት ዝናብ ፈጽሞ አልጀመረም ተብሏል። በዝናብ እጥረቱ ምክንያት እንስሳት ለግጦሽና መኖ እጥረት ሲጋለጡ፣ ነዋሪዎችም ለመጠጥ ውሃ ከፍተኛ እጥረት እያጋጠማቸው መሆኑ ተገልጿል። በ21 ቀበሌዎቹ የሚኖሩ ነዋሪዎች ራሳቸውንና እንስሳቶቻቸውን ከከፋ አደጋ ለመታደግ የመንግሥትና የሰብዓዊ ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ ጠይቀዋል። በተለይም በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ላለፉት ስድስት ዓመታት በኤርትራ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗