በጻድቃኔ ማርያም ገዳም በደረሰ ድንገተኛ ርዕደ መሬትና
በጻድቃኔ ማርያም ገዳም በደረሰ ድንገተኛ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ በታላቋ ገዳም በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ከክረምቱ መግባትና ከከፍተኛ ዝናብ ጋር ተያይዞ በተከሰተ ድንገተኛ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ወገኖች ሕይወት አልፏል። ለጸበል፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫዎች ተሰብስበው በነበሩ ምዕመናን ላይ በደረሰው በዚህ ልብ ሰባሪ አደጋ ተጨማሪ 5 ሰዎች ላይ ከፍተኛና መለስተኛ ጉዳቶች መድረሳቸው ተገልጿል። የሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ ወዲያውኑ በስፍራው በመገኘት ለሞቱ ወገኖች ጸሎተ ፍትሐት ያደረጉ ሲሆን፣ ለተጎዱትና ላዘኑት ምዕመናን አባታዊ ጽናትን ሰጥተዋል።
Read the full story at brook_news_ethiopia ↗