በመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-03 13:40:08 UTC
AdYour ad here[email protected]

በመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው ታላቋ የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬት እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ምዕመናን ሕይወት ማለፉን የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ። በተከሰተው በዚህ አሰቃቂ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት፣ እንዲሁም በ2 ሰዎች ላይ መለስተኛ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል። የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን መሪር ሐዘን ገልጿል። አደጋው ከተከሰተበት ቅጽበት ጀምሮ የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሃን ተስፋን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት በስፍራው በአካል በመገኘት ነፍስ የማዳን ሥራውን በበላይነት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]