"የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የ14 ሰዎች ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል" - የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-03 16:47:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

"የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የ14 ሰዎች ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል" - የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ አደጋው መከሰቱን ገልጾ፣ ወደ ቦታው የተቀናጀ ቡድን ማሰማራቱን ነግሮናል። የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቃጥበብ አባቡ በሰጡን ቃል፣ "ድንገተኛ አደጋ ነው የተከሰተው። ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የዝናብ፣ የመብረቅ ድምፅ ስለነበረ በዚያ ሳቢያ ነው የመሬት መንሸራተቱ ያጋጠመው" ብለዋል። "14 ምዕመናን ሕይወታቸው አልፏል።…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]