ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከ805 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ተከልኩ አለች
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከ805 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ተከልኩ አለች ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ይፋዊ እቅድ በመያዝ "805.3 ሚሊዮን" ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ እቅድ በላቀ ስኬት ማጠናቀቋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳውቀዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በንቃት በተሳተፉበት በዚህ ግዙፍ የንቅናቄ መርሃ ግብር ሀገሪቱ ታላቅ ድምቀት ያለው ድል አስመዝግባለች። ይህ ታሪካዊ ድል የዕለቱ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የያዘችውን የረጅም ጊዜ እቅድ ያለምንም መጓደል በተግባር እያሳካች መሆኗን በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗