ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ እና የሕግ ባለሙያው አበራ ንጉሥ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼
ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ እና የሕግ ባለሙያው አበራ ንጉሥ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼ በወቅታዊ ጉዳዮች ትንታኔ በመስጠትና በፓርቲ ፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው የሚታወቁት አቶ አበበ አካሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ። ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ግቢ ውስጥ እንደሚገኙ አንዳፍታ ጠቅሷል። በሌላ በኩል፣ የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ጠበቃ የሆኑት አቶ አበራ ንጉሥ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸው ተሰምቷል። አቶ አበራ ትናንት ጧት 1፡30 ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው የተወሰዱ ሲሆን፣ ፖሊስ ሁለት የእጅ ስልኮቻቸውን ከመውሰድ ውጭ ፍተሻ እንዳላደረገ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል። የሕግ ባለሙያው አዲሱን የፖለቲካ ፓርቲ በማደራጀት ሂደት ላይ ይገኙ እንደነበር ተጠቅሷል።…
Read the full story at wasulife ↗