የክረምት ተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች ይፋ ሆኑ‼

WASULIFEneutral2026-08-04 08:58:12 UTC
AdYour ad here[email protected]

የክረምት ተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች ይፋ ሆኑ‼ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው የክረምት ወቅት በተረኛ ችሎት የሚስተናገዱ አጣዳፊ ጉዳዮችን ይፋ አደረገ። በዚሁ መሠረት በፍትሐ ብሔር በኩል፦ 📌አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች 📌 የልጅ ቀለብ፣ አካል ነጻ የማውጣት እና የእንቅስቃሴ ገደብ አቤቱታዎች 📌 የሰራተኞች የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸም እና የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች በወንጀል በኩል ደግሞ፦ 📌የዋስትና፣ የአመክሮ፣ የእስረኛ መዛግብት (አርቲዲ) እና የሰበር አቤቱታዎች 📌 የአራዳ ምድብ ችሎት ጊዜ ቀጠሮ እና ለመሰየም የሚቀርቡ አቤቱታዎች የሚስተናገዱ ይሆናል። ፍርድ ቤቱ ተገልጋዮች ይህንን አሠራር ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]