የሱማሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የኬንያ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-04 10:00:30 UTC
AdYour ad here[email protected]

የሱማሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የኬንያ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ የሱማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጅብሪል አብዲራሺድ ሀጂ ከጉዞ ሰነዳቸው ጋር በተያያዘ በተነሱ ጥያቄዎች ምክንያት ከናይሮቢ አየር ማረፊያ ከተባረሩ ከሳምንታት በኋላ የኬንያ ፓስፖርታቸውን እና የልደት የምስክር ወረቀታቸውን በሞቃዲሾ ለሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ ማስረከባቸውን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ጅብሪል ፓስፖርታቸውን ያስረከቡት በፈቃደኝነት እና “ለሱማሊያ ያላቸውን ታማኝነት” እንዲሁም ቁርጠኝነት ለማሳየት እንደሆነ ተናግረዋል። ፓስፖርቱ በህጋዊ መንገድ የተገኘ እና ከኬንያ ህግ ጋር በተጣጣመ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ውሳኔው በኬንያ ባለስልጣናት በተጠየቀ ጥያቄ ወይም በነበረ አለመግባባት ምክንያት የተደረገ አይደለም ብለዋል። @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]